ጤናዎ። ህይወትዎ።

የጤና መድህንዎን ሲታመሙ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ሊጠቀሙት ይችላሉ። ነገር ግን ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ የጤና እንክብካቤን ማግኘት ይበልጥ ጠቃሚ ነው።

መደበኛ የሆኑ የአጠቃላይ ህክምና፣ የጥርስ ህክምናና የአይን ህክምና ምርመራዎች ስለ ጤናዎ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁና ለተወሰኑ በሽታዎች ያለዎትን ተጋላጭነት እንዲረዱ እንዲሁም ሳያስተውሏቸው ሊተላለፉ የሚችሉ የበሽታ ምልክቶችን እንዲያስተውሉ እድል ይሰጡዎታል። መደበኛ ምርመራዎች የጤና ችግሮችን ወደ ከባድ ችግር ከመለወጣቸው በፊት ለማወቅና ለማከም ይረዳሉ።

ነጻ የመከላከል አገልግሎቶች

የመከላከል ህክምናዎች በጣም ጠቃሚ ስለሆኑ እነዚህ ህክምናዎች በአመት አንድ ጊዜ ምንም ተጨማሪ ወጪ ሳያወጡ ለእርስዎ ይሰጣሉ። ይህም ማለት የጋራ-ክፍያም ሆነ የጋራ-ኢንሹራንስ አይከፍሉም። ምንም እንኳን ለአመቱ የሚደርስብዎትን ተቀናሽ ከፍለው ባይጨርሱም የመከላከል ህክምናዎች አሁንም ለእርስዎ ነጻ ናቸው።

 • የወሊድ መቆጣጠሪያ
 • የደም ግፊት ክትትል
 • የጡት ካንሰር ምርመራ (ማሞግራም (mammogram))
 • የኮሌስትሮል ምርመራ
 • የኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ምርመራ
 • የድብርት (Depression) ምርመራ
 • የስኳር ህመም (Diabetes) ምርመራ
 • የእጽ፣ የአልኮል እና የቶባኮ አለአግባብ መጠቀም የምክር አገልገሎት
 • የጉንፋን መርፌዎች (Flu shots)
 • የኤችአይቪና የአባላዘር በሽታዎች ምርመራና የምክር አገልግሎት
 • ተደጋግመው የሚሰዱ ክትባቶች

ከእድሜዎና ተጋላጭ ከሚያደርጉዎት ነገሮች ጋር Happy Etheopian family relaxing togetherየተያያዙ የተወሰኑ ገደቦች አሉ። የነጻ የመከላከል ህክምናዎን በተመለከተ ሙሉ ዝርዝር ለማግኘት HealthCare.gov/preventive-care-benefits ድረ ገጽን ይጎብኙ።