እንዴት የጤና ጥበቃ እንክብካቤ ማግኘት እንደሚቻል

Smiling senior african man talking to nurse.አሁን የጤና መድህን ሽፋን ስላለዎት የሚያስፈልግዎትን የጤና ጥበቃ እንክብካቤ በማግኘት የሚቻለውን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑ እርግጠኛ ይሁኑ። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ዶክተር ቢሮ፣ ወደ ክሊኒክ ወይም በማህበረሰብዎ ውስጥ ወዳለ የአስቸኳይ የጤና እንክብካቤ መስጫ መሄድዎ ጥሩ ምርጫ ነው። በአጠቃላይ በዶክተር ቢሮ ወይም በክሊኒክ ውስጥ በጣም ያነሰ ገንዘብ የሚከፍሉ ሲሆን በመጠበቂያ ክፍል ውስጥም የሚያጠፉት ጊዜ በጣም ትንሽ ነው።

ወደ ድንገተኛ ክፍል ሲሄዱ

እውነተኛ የሆነ ድንገተኛ ህመም ካጋጠመዎ ወደ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ። ስልክ የመደወያ ጊዜ ከሌለዎት ህመምዎ እውነተኛ የሆነ ድንገተኛ ህመም ስለሆነ ወደ ድንገተኛ ክፍል መሄድ አለብዎ። ያለበለዚያ ለጤና እንክብካቤዎ የት መሄድ እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ይህንኑ ለማወቅ ወደ ጤና አገልግሎት ሰጪዎ ወይም ወደ ኢንሹራንስ ድርጅትዎ ነርስ ይደውሉ።

የጤና ጥበቃ እንክብካቤ ለማግኘት መውሰድ ያለብዎት እርምጃዎች እነዚህ ናቸው

1) ምን አይነት የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሰጪ እንደሚፈልጉ ይወስኑ። በርካታ አይነት የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሰጪዎች አሉ። አንዳንድ ዶክተሮች የተወሰኑ አይነት በሽታዎች ላይ የሚያተኩሩ (ስፔሺያሊስቶች) ናቸው። አንዳንድ ዶክተሮች አጠቃላይ የጤና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ሲሆኑ አንዳንዶች ደግሞ ዶክተሮች ያልሆኑ የዶክተር ረዳቶች ወይም ነርሶች ቢሆኑም ብዙ ስልጠና የወሰዱና በጣም ጥሩ የሆነ የጤና ጥበቃ እንክብካቤ የሚሰጡ ናቸው።

የተለያዩ ተቀዳሚ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎች

  • አጠቃላይ ሃኪም
  • የቤተሰብ ሃኪም
  • የውስጥ ደዌ
  • የጽንስና የማህጸን ህክምና (OB/GYN) (የሴቶች ጤና አገልግሎት ብቻ)
  • ጄሪያትሪሽያን (Geriatrician) (ለአዛውንት የሚሰጥ ህክምና)
  • የህጻናት ህክምና (Pediatrician) (ለህጻናት)
  • ነርስ
  • የሃኪም ረዳት

ስለ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ፍላጎቶችዎ ያስቡና ተቀዳሚ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎ—ወይም ዋና የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎ ማን እንዲሆን እንደሚፈልጉ ይወስኑ። በተጨማሪም ስለሚከተሉት ጉዳዮች ያስቡ፦ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሰጪዎ የት እንዲሆን ይፈልጋሉ? ማታ እና የሳምንት መጨረሻ ቀናት ብቻ ነው የሚመችዎት? አገልግሎት ሰጪዎ የተወሰነ ቋንቋ እንዲናገር ይፈልጋሉ? አገልግሎት ሰጪዎ ከእርስዎ ጋር ተመሳሳይ ጾታ እንዲኖው ይፈልጋሉ?

2) ኢንሹራንስዎን የሚቀበሉ አገልግሎት አቅራቢዎችን ይፈልጉ። በመቀጠል የእርስዎን መስፈርቶች የሚያሟሉና ኢንሹራንስዎን የሚቀበሉ የጤና አገልግሎት ሰጪዎችን ይፈልጉ። በኢንሹራንስ ካርድዎ ላይ ያለውን የአባላት አገልግሎት ቁጥር በመደወል ወይም የኢንሹራንስ ድርጅትዎን ድረ ገጽ በመጎብኘት ይህንን ማወቅ ይችላሉ። አማራጮችዎን ይዘርዝሩና ከዚያም በቅደም ተከተል ያስቀምጧቸው። ስለ እነሱ መረጃዎችን በማጥናት የትኛዎቹን ይበልጥ እንደሚወዷቸው ማወቅ ይችላሉ—ግምገማዎችን ያንብቡ እንዲሁም ጥቆማዎችን ለማግኘት ከጓደኞችዎና ከቤተሰብዎ ጋር ይነጋገሩ።

3) አገልግሎት አቅራቢ ይምረጡና ቀጠሮ ያስይዙ። እስከሚታመሙ ድረስ አይጠብቁ። ወደ አገልግሎት አቅራቢው ይደውሉና አሁኑኑ ቀጠሮ ያስይዙ። አዲስ ታካሚ ሲሆኑ ቀጠሮ ለመያዝ አንድ ወይም ሁለት ሳምንት መጠበቅ ሊኖርብዎ ይችላል። ቀጠሮ ለመያዝ ሲደውሉ በስልክ ለሚያናግርዎት ሰው አዲስ ታካሚ እንደሆኑ ያሳውቁና ኢንሹራንስዎን ይቀበሉ እንደሆን ያረጋግጡ።

 4) ወደ ቀጠሮዎ ይሂዱ። ለእርስዎ ትክክለኛ የሆነውን ቦታና የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢ ከመረጡ በኋላ ምቾት እንዲሰማዎት ግለሰቡን ለማወቅ ይሞክሩ። ከጤና ጥበቃ አገልግሎቱ የሚፈልጉትን በማሰብና የእርስዎንና የቤተሰብዎን የጤና ታሪክ በማስታወስ ለመጀመሪያ ቀጠሮዎ ይዘጋጁ። ቀጠሮዎ አጭር ሊሆን ይችላል። ከመሄድዎ በፊት ጥያቄዎችዎንና ያሉዎትን ስጋቶች በማዘጋጀት ከጤና አገልግሎት አቅራቢዎ ጋር ያለዎትን ጊዜ በአግባቡ ይጠቀሙበት። አገልግሎት አቅራቢውን ካልወደዱት ከላይ በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተጠቀሱትን በመድገም ሌላ አገልግሎት አቅራቢ መቀየር ይችላሉ።

 5) ጤንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆይና ማናቸውም የጤና ችግሮች ላይ በጊዜ ለመድረስ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ምርመራ ያድርጉ። አመታዊ ምርመራዎች እርስዎ ላይ ምንም ተጨማሪ ወጪ እንደማያስከትሉ ያስታውሱ።

አንድ ዋና የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢ ወይም ተቀዳሚ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢ ሊኖርዎ ይገባል። ሆኖም ግን በለሌሎች ቦታዎች የጤና አገልገሎቶችን ሊያገኙ ይችላሉ። እርስዎና ቤተሰብዎ በየትኛዎቹ ቦታዎች የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዳገኙ ለመከታተል በዚህ ሰነድ ጀርባ ላይ ያሉትን ገጾች ይጠቀሙ።