የገንዘብ ጉዳይ: ለጤና ጥበቃ የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን

የጤና መድህን ሽፋን የተወሳሰበ ነገር ቢሆንም በጣም ጠቃሚ ነገር ነው። ለጤና መድህን ሽፋንና ለጤና ጥበቃ አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ ግራ ሊያጋባዎ ይችላል። የሚከፍሉባቸው ሶስት መሰረታዊ መንገዶች አሉ።

አረቦን (Premium): ይህ ለኢንሹራንስ ድርጅትዎ በመደበኝነት የሚከፍሉት ክፍያ ነው። ልክ እንደ አባልነት ክፍያ ነው። ይህንን ክፍያ በየወሩ በጊዜው መክፈል በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ክፍያን ሳይከፍሉ ከቀሩ የመድህን ሽፋንዎን ሊያጡ ይችላሉ።

የጋራ-ክፍያ (Co-Pay): ይህ የጤና አገልግሎት ሲያገኙ የሚከፍሉት ክፍያ ነው። የጤና አገልግሎት ማለት ዶክተርን ከመጎብኘት ጀምሮ በማዘዣ የሚወሰዱ መድሃኒቶችን እስከመቀበል ሊደርስ ይችላል። የጋራ-ክፍያዎ በሚወስዱት የአገልግሎት አይነት ላይ ተመስርቶ የተወሰነ ቁርጥ ክፍያ ነው: የመጀመሪያ ደርጃ ህክምና ጉብኝት፣ ልዩ (specialty) ህክምና ጉብኝት፣ መድሃኒት፣ የድንገተኛ ክፍል ህክምና ወይም የሆስፒታል ጉብኝት ወዘተ። አብዛኛዎቹ የጋራ-ክፍያዎች በአገልግሎቱ ላይ በመመስረት በ $5 እና $30 መካከል ናቸው።
የድንገተኛ ክፍልና የሆስፒታል የጋራ-ክፍያዎች ይበልጥ ውድ ናቸው። እስከ $300 ድረስ ሊደርሱ ይችላሉ። የጋራ-ክፍያዎችዎ በኢንሹራንስ ካርድዎ ላይ ተዘርዝረዋል። ካላገኟቸው እገዛ ለመጠየቅ የአባላት አገልግሎት ቁጥሩ ላይ ይደውሉ።

የጋራ-ኢንሹራንስ (Co-Insurance): ይህም የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሲያገኙ የሚከፍሉት የገንዘብ መጠን ነው። ከአጠቃላዩ የህክምና ወጪ የእርስዎን ድርሻ የሚያመልክት እንጂ መደበኛ ክፍያ አይደለም። ለተቀረው ወጪ ሂሳቡ ለኢንሹራንስዎ ይላካል። ነገር ግን እርስዎ ተቀናሹን ከፍለው እስካልጨረሱ ድረስ ኢንሹራንሱ አይከፍልም። ኢንሹራንሱ ለአገልግሎቱ ካልከፈለ ሂሳቡ ለእርስዎ ይላካል።

የጋራ-ክፍያ እና የጋራ-ኢንሹራንስ ልዩነት:

ለአንድ የጤና አገልግሎት የሚደርስብዎትን የጋራ-ኢንሹራንስ ከማወቅ ይልቅ የጋራ-ክፍያውን ማወቅ ይቀላል። አጠቃላይ የአገልግሎቱ ወጪ እንዲሁም ያልትከፈለው ተቀናሽ ቀሪ መጠን ምንም ያህል ቢሆን የጋራ-ክፍያው የተወሰነ ቁርጥ የገንዘብ መጠን ነው። የጋራ-ኢንሹራንስ ግን ከአጠቃላይ የአገልግሎቱ ወጪ የተወሰነ መቶኛ ክፍያ ነው።

ተቀናሽ (Deductible): ይህ ኢንሹራንስዎ መክፈል ከመጀመሩ በፊት በየአመቱ መክፈል ያለብዎት መጠን ነው። የጤና አገልግሎት ሲቀበሉ የጋራ-ክፍያ ይከፍላሉ። ይህ የከፈሉት ክፍያ ከአጠቃላይ የአገልግሎቱ ክፍያ ላይ ይቀነስና ክፍያ መጠየቂያው ለመድህን ድርጅትዎ ይላካል። ለአመቱ የሚጠበቅብዎትን ተቀናሽ ክፍያ ከፍለው ከጨረሱ የመድህን ድርጅቱ ቀሪውን ክፍያ ይከፍልና በዚያ ጉዳዩ ይዘጋል። ተቀናሽዎን ከፍለው ካልጨረሱ መድህን ድርጅትዎ ቀሪውን ክፍያ የሚከፍል ሲሆን የጤና አገልግሎት አቅራቢዎ ሂሳብ መጠየቂያውን ለእርስዎ ይልካል። የመድህን ድርጅትዎ ተቀናሽዎን ከፍለው መጨረስዎንና እነሱ መክፈል መጀመር እንዳለባቸው ለማወቅ እነዚህን የገንዘብ መጠኖች በመመዝገብ ይከታተላሉ።

Deductible Chart AMH

በአጠቃላይ ዝቅተኛ ወርሃዊ የአረቦን ክፍያዎች ያላቸው የኢንሹራንስ እቅዶች ኢንሹራንስ ድርጅቱ መክፈል ከመጀመሩ በፊት በእያንዳንዱ አመት ከፍለው መጨረስ ያለብዎት ከፍተኛ የሆኑ ተቀናሾች ይኖራቸዋል። ከፍተኛ የሆነ የአረቦን ክፍያ ያላቸው ኢንሹራንሶች ዝቅተኛ ተቀናሾች አላቸው።

የኢንሹራንስ ካርድዎ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ቲኬትዎ እንደሆነ ያስታውሱ። የጤና አገልግሎት ሲያስፈልግዎ እጅዎ ላይ እንዲኖር ሁልጊዜም ይዘውት ይንቀሳቀሱ።