ለምርመራዎ መዘጋጀት

መደበኛ የሆኑ የህክምና ምርመራዎች የጤና ችግሮችዎ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው መፊት ለማወቅና ለማከም ይረዳሉ። ምርመራዎች ብዙ ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎች ናቸው የሚባሉት ከመታመም ስለሚያድኑዎ ወይም የጤና ችግሩ ከመባባሱ በፊት መፍትሄ እንዲገኝለት ስለሚያደርጉ ነው።

ከምርመራዎችዎ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መከተል ያለብዎት ቀላል ቅደም ተከተሎች የሚከተሉት ናቸው፦

1) ስለ የግል የጤና ፍላጎትዎ ያስቡ። ከጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢ ጉብኝትዎ ማግኘት የሚፈልጉት ምንድን ነው?

2) በቀጠሮው ወቅት መጠየቅ የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎችና ማውራት የሚፈልጉባቸውን ጉዳዮች ዝርዝር ያዘጋጁ።

3) ስለ የግል የጤና ታሪክዎ ይወቁ።

  • አለርጂዎች
  • አሁን ያለ ህመም
  • የክትባት ሪከርድ
  • የህጻንነት ወቅት ህመሞች
  • ቀዶ ጥገናዎች
  • የግል ልምዶች ((ለምሳሌ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምዶች፣ የአመጋገብ ልምዶች፣ የሲጋራና የአልኮል አጠቃቀም)

4) ስለ ቤተሰብዎ የጤና ታሪክ ይወቁ። ለምሳሌ ከቅርብ ዘመዶችዎ ውስጥ የሚከተሉት ህመሞች ኖሮባቸው ያውቃል፦

  • ካንሰር
  • የልብ ህመም
  • ስትሮክ
  • ስኳር ህመም

5) ከጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎ ጋር የተነጋገሩትን ነገር ለማስታወስ እንዲያግዝዎ ማስታወሻ ይያዙ።

6) የራስዎ ቀጠሮ መሆኑን ያስታውሱ። ጥያቄዎችን ለመጠየቅና የጤና አገልግሎት አቅራቢው የተናገረው ነገር ካልገባዎ እንዲደግምልዎ መጠየቅ አይፍሩ።

Portrait of young Etheipian boy with his mother.ወደ ሃኪም ቤት የሄዱት ለምርመራም ይሁን በህመም ምክንያት ከዚያ በኋላ ወደ ላብራቶሪ መሄድና መድሃኒት መውሰድ የመሳሰሉ ማድረግ የሚገባዎ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ከቀጠሮው ከመውጣትዎ በፊት ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ማወቅዎን እርግጠኛ ይሁኑ። እርግጠኛ ካልሆኑ መጠየቅ አይፍሩ።

የእኔ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎች ። ይህንን ቅጽ እርስዎና ቤተሰብዎ የጤና እንክብካቤ ለማግኘት ከየት እንዳገኙ ለመከታተል ይጠቀሙበት።

የግልና የቤተሰብ የጤና ታሪክ ። የእርስዎንና የቅርብ የቤተሰብ አባላትዎን የጤና ታሪክ ማወቅ ለእርስዎና ለጤና ጥበቃ አገልግሎት ሰጪዎ ጠቃሚ ነገር ነው።

የእኔ መድሃኒቶች ። የሚወስዷቸውን መድሃኒቶችና የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅራቢዎ የሚያደርጋቸውን ማናቸውንም ለውጦች ለመከታተል ይህንን ቦታ ይጠቀሙ።